ቀዳሚቃል

አጼምኒልክበታሪክሲታወሱከሚኖሩባቸውክንዋኔዎችአንዱበ19ኛውመቶዓመትየመጨረሻሩብባሉትዓመታትየኢትዮጵያንግዛትከመቼውምበበለጠመጠንአስፍተውዘመናዊቷንኢትዮጵያለመፍጠርመቻላቸውነበር።ይህሂደትበቀላሉየተከናወነአልነበረም።የተወሰኑግዛቶችበሰላምሲገብሩላቸውሌሎችግንአሻፈረኝበማለታቸውብዙእልቂትናእንግልትንያስከተለየጦርዘመቻአስከትሎነበር።ከዚያምባሻገርበተለይበመጨረሻዓመታትየተደረጉትየግዛትማስፋፋትዘመቻዎችዙሪያውንከበውከተቆናጠጡባቸውየቅኝግዛቶችወደኢትዮጵያድምበርለመስፋፋትካኮበኮቡትየቅኝግዛትኃይሎችጋርምመፋጠጥናአንዳንዴምመፋለምነበረበት።
ይህፍጥጫናፍልሚያለጊዜውምቢሆንሊረግብየቻለውእ.አ.አ. ከ1897 ጀምሮእስከ 1908 ድረስባሉትዐሠርትዓመታትምኒልክከአጎራባችቅኝገዥዎችጋርየኢትዮጵያንድንበርሲያካልሉነው። በዚህምረገድ በ1897 ጅቡቲንከተቈጣጠሩትፈረንሣዮችጋር፣ በዚሁዓመትየእንግሊዝሶማሊላንድንከተቈጣጠሩትእንግሊዞችጋር፣ በ1900፣ 1902 እና 1908 ደግሞኤርትራንየራሳቸውካደረጉትጣሊያኖችጋር፣ በ1902 የተንጣለለውንየሱዳንግዛትበግብጽስምእናስተዳድራለንብለውራሳቸውንከሰየሙትከእንግሊዞችጋር፣ በ1907 የኢጣልያሶማሊላንድንቅኝካደረጉትኢጣልያኖችጋር፣ እና በ1908 የብሪቲሽኢስትአፍሪቃየሚልስያሜሰጥተውኬንያንናኡጋንዳንከሚያስተዳድሩትጋርእንግሊዞችጋርየድንበርውልተዋዋሉ።
እነዚህንበድምሩስምንትየሆኑየድንበርውልመካለሉበዘመኑከነበረውየጂዎግራፊዕውቀትናየአስተዳደርብቃትአንጻርለምኒልክምንያህልከባድእንደነበረመገመትአያዳግትም። ብዙውንጊዜበተቻለመጠንከአካባቢውባላባቶችናሽማግሌዎችየኢትዮጵያንትክክለኛየወሰንክልልለማወቅቢሞከርምይህሁሌይሳካነበርማለትአይደለም። በዚህረገድፈረንጆቹአንጻራዊየበላይነትነበራቸውማለትይቻላል። ምክንያቱምቀደምሲልባገርጒብኝትስምበየድንበሩሲንቀሳቀሱየነበሩዜጎቻቸውየአካባቢውንጂዎግራፊዘርዝሮየሚያስረዳሪፖርትናመጻሕፍትበመጻፋቸውነበር።
ያምሆኖወሰንንካርታላይአስፍሮፊርማናማኅተምማኖሩየነገርመጀመሪያውእንጂመጨረሻውአልነበረም። ያ ካርታላይየተሣለውሥዕልመሬትላይመተርጐምነበረበት፤ ማለትምድንበሩበማያሻሙናጉልህበሆኑምልክቶችመደንገግነበረበት። የመጀመሪያውሂደትቀላሉ፣ በእንግሊዝኛአጠራሩ«ዲሊሚቴሽን»የሚባለውሲሆን፣ ሁለተኛውከባዱናውስብስቡ፣ በእንግሊዝኛአጠራሩ«ዲማርኬሽን»የሚባለውነው። ለነዚህሁለትቃላትሁነኛየአማርኛአቻማግኘትያዳግታል። የሚፈጠረውንየሐሳብመደናገርለመቀነስግን፣ የመጀመሪያውን«መካለል»፣ ሁለተኛውን«መደንገግ»ብሎመጥራትይቀልይሆናል። በመግቢያውላይየተጠቀሰውየደራሲውቅኔ («ከሕግቤትገብቶምነውቢወሰን»፣ ማለትምቢደነገግ) ለዚህየቃላትምርጫድጋፍየሚሰጥይመስላል።
የኢትዮጵያናየአጎራባችቅኝግዛቶችድንበሮችዋነኛውችግርሁለተኛውሂደትየመጀመሪያውንበፍጥነትአለመከተሉወይምበአወዛጋቢሁኔታመከናወኑነው። ለዚህምክፍተትየተለያዩምክንያቶችነበሩ። አንደኛውድንበሩንለመደንገግበኢትዮጵያበኩልቅኝገዥዎችማሰማራትየቻሉትንባለሙያዎችየሚመጥኑባለሙያዎችማሰማራትአለመቻልነው። ይህከሱዳንናከኬንያጋርበተደረገውየወሰንመደንገግሂደትበጉልህታይቷል። በመሆኑምእንግሊዞችግዊንየተባለውእንግሊዛዊብቻውንየደነገገውወሰንሕጋዊውወሰንነውሲሉ፣ የኢትዮጵያመንግሥትግንለባለሙያውሕጋዊውክልናስላልሰጠውየሱንድንጋጌአልቀበለውምሲልቆይቷል። ይህም በ1960ዎቹና በቅርብዓመታትምየኢትዮጵያንናየሱዳንንወሰንአወዛጋቢእንዲሆንያደረገውንሁኔታአስከትሏል።
በሚያስገርምሁኔታከዚህተቃራኒየነበረውደግሞየኢጣልያመንግሥትበሰሜኑክፍልበኤርትራናበደቡብምሥራቅደግሞበሶማሌግዛቱናበኢትዮጵያመካከልየነበሩትንወሰኖችለመደንገግያሳየውዳተኛነትነው። በተለይምየኤርትራናየኢትዮጵያንወሰንበተመለከተየኢትዮጵያመንግሥትካንዴምሁለቴ (በተለይእ.አ.አ. በ1920ዎቹ ማገባደጃላይ) ወሰናችንንበተገቢውመንገድእንደንግግብሎቢወተውትምጆሮዳባልበስብሎበዝምታአልፎታል። ኋላገሃድሆኖእንደወጣው፣ የዚህምክንያቱየኢጣልያመንግሥትየሩቅጊዜግብኢትዮጵያንወሮከሁለቱቅኝግዛቶቹለመጠቅለልስለነበር፣ ወሰኑንበመደንገግይህንትልሙንለማጨናገፍአልፈለገም። የዚህጦስግንኢጣልያምከአካባቢውተባራ፣ ከረጅምዘመንጦርነትበኋላኤርትራነፃመንግሥትስትሆንሁለቱአገሮችያልተደነገገድንበርስለወረሱይኸውየቅርብጊዜትዝታችንየሆነውንየድንበርጦርነትናእስካሁንምእልባትያልተገኘለትቀዝቃዛጦርነትአስከትሏል። (ይህማለትግንየወሰንጭቅጭቁየጦርነቱብቸኛመነሾማለትእንዳልሆነይታወቅ።)
ከዚህአንጻርሲታይአሁንለአንባቢበቀረበውመጽሐፍውስጥበዝርዝርየተገለጸውየኢትዮጵያናየእንግሊዝሶማሊላንድየወሰንመደንገግታሪክየተለየአብነትአለው። ይኸውምወሰኑመደንገጉብቻሳይሆንሂደቱበሚያስገርምምልኣትናጥንቃቄመተረኩነው። መተረኩብቻሳይሆንትረካውከኢትዮጵያወገን፣ በኢትዮጵያዊቋንቋመሆኑነው። ምክንያቱምበተለይየሱዳንንናየኬንያንወሰንድንጋጌአስመልክቶቀደምሲልእንደዚህዓይነትተመሳሳይዘገባበእንግሊዞችእንጂበኢትዮጵያውያንባለመቅረቡነው። ያምሆኖየእንግሊዞቹዘገባበዚህመጽሐፍየተካተተውንዘገባምልኣትአለውብሎደፍሮለመናገርያዳግታል።
ለዚህየተለየሁኔታጉልህአስተዋፅኦካደረጉትመካከልየወሰኑመደንገግከመካለሉሠላሳሰባትዓመትያህልዘግይቶመከናወኑነው። በመሆኑምበመሃሉባሉትዓመታትኢትዮጵያከቅኝገዥባለሙያዎችጋርእኩልመደራደርየሚችሉኢትዮጵያውያንባለሙያዎችለማፍራትናየአስተዳደርዘይቤዋንምበመጠኑምቢሆንለማዘመንችላለች። በኢትዮጵያበኩልየመደንገግሥራውንበበላይነትይቈጣጠሩየነበሩትየሥራሚኒስትሩፊታውራሪታፈሰሀብተሚካኤልሲሆኑ፤ የኮሚሲዮኑመሪበጅሮንድተሰማባንቴ፣ ረዳቶቻቸውደግሞብላታዘውዴበላይነህእናአቶ (ኋላብላቴንጌታ) ሎሬንዞታእዛዝነበሩ። በተጨማሪምበሦስተኛረዳትተካላይነትናየቴክኒክሹምነትሙሴላሪቪዬርየተባለፈረንሳዊናአራትየዦኤዴዝናየቶፖግራፊመሐንዲስየሆኑየውጭአገርባለሙያዎችበኮሚሲዮኑተካተውነበር።
ሌላውበኔግምትለሁኔታውከፍተኛአስተዋፅኦያደረገውደግሞብላታመርስዔኀዘንንየመሰለጥንቁቅምሑርየኮሚሲዮኑዋናጸሐፊሆነውመመደባቸውነው። እሳቸውበጥንቃቄያደራጁትናይዘውያቆዩትዘገባናአባሪሰነዶችናቸው (በአዘጋጁጥረትከተሰበሰቡትአባሪዎችጋርበመሆን) አሁንለኅትመትየበቁት። አሥራአራትወራትየፈጀውናብዙአደጋዎችናፈተናዎችየተጋረጡበትየድንበርመደንገግሥራቀላልእንዳልነበረከዘገባውመረዳትይቻላል። መጽሐፉንተጨማሪዋጋየሚያሰጠውደግሞየጋራኮሚሲዮኑያካሄዳቸውንሐያስድስትዋናስብሰባዎችፕሮሴቬርባልማካተቱነው። እነዚህበኮሚሽነሮቹናረዳትኮሚሽነሮቹየተፈረሙትናአልፎአልፎምአግባብነትባላቸውካርታዎችየታጀቡትፕሮሴቬርባሎችድርድሩንበዝርዝርለመከታተልትልቅጠቀሜታአላቸው። ብላታትተውልንየሄዱትየአማርኛውንፕሮሴቬርባልብቻሲሆን፣ አዘጋጁየእንግሊዝኛውናየአማርኛውፍቺጐንለጐንየተቀመጡበትንሰነድከእንግሊዝብሔራዊቤተመዛግብትለማግኘትባደረገውጥረትአንባቢየተሟላሰነድለማግኘትበቅቷልማለትይቻላል።
የታሪክምፀትሆነናውዝግብንያስወግዳልተብሎየታቀደውየወሰንመደንገግሂደትበወሰንግጭትየታጀበሆነ። ይኸውም ለ1928ቱ የፋሽስትኢጣልያወረራሰበብየሆነውየወልወልግጭትነው። በመሠረቱየግጭቱመነሾከወሰንኮሚሽኑሥራጋርየተያያዘአልነበረም። የግጭቱስፍራምበኢትዮጵያናበኢጣልያሶማሊላንድመካከልእንጂእየተደነገገባለውበኢትዮጵያናበእንግሊዝሶማሊላንድመካከልአልነበረም። ይሁንእንጂየኮሚሽኑአባላትሳያስቡትበነገሩተጠልፈውየተኲሱተቋዳሽለመሆንበቁ። ከታሪክአንጻርየዚህአጋጣሚዋናፋይዳስለግጭቱመነሾናሂደትከኢትዮጵያወገንዘርዘርያለመረጃለማግኘትመቻላችንነው።
ለረጅምዓመታትብላታመርስዔኀዘንየሚታወቁትየሁላችንምየሰዋስውአፍመፍቻበነበረውየአማርኛሰዋስውበተሰኘውመጽሐፋቸውነበር። ከቅርብዓመታትወዲህግንየምሑሩያልታተሙሥራዎችለኅትመትበመብቃታቸው፤ አንባቢስላገሩታሪክ፣ በተለይምስለሐያኛውመቶዓመትመጀመሪያአጋማሽብዙመረጃዎችለማግኘትታድሏል። በዚህረገድ በ1999 የሐያኛውመቶዓመትመባቻበሚልርዕስየታተመውትዝታቸውፈርቀዳጅነውለማለትይቻላል። ልጃቸውአምኃመርስዔኀዘንከዚያንጊዜጀምሮያልታተሙሥራዎቻቸውንበተከታታይአደራጅቶለኅትመትበማብቃቱልፋታቸውመናእንዳይቀርከማድረጉበተጨማሪአንባቢብዙዕውቀትእንዲሸምትረድቷል። ይህአሁንለኅትመትየበቃውመጽሐፍምበተሟላሁኔታእንዲወጣአያሌአባሪዎችንበማከልናየሁለቱንምወገንተዋናዮችንየሕይወትታሪክባጭርባጭሩበማቅረብለሠራውሥራምስጋናይገባዋል። እንደዚሁ፣ ቀሪዎቹያልታተሙየብላታሥራዎችምብዙምሳይርቅለብርሃንይበቃሉብለንተስፋእናደርጋለን።
ባሕሩዘውዴ
በአዲስአበባዩኒቨርሲቲየታሪክኤሜሪተስፕሮፌሰር