ትዝታዬ ስለራሴ የማስታውሰው

rsz_book_2_use_this

. . . የዘመኑ አብነት የሆኑ ሰዎች እየተነሡ ለብዙ ነገር መረጃ የሰጡ፥ ብዙ ግንዛቤም የሚገኝበትን ጽሑፍ የዘገቡልን ሰዎች ይገኛሉ። የአለፉት ዘመናት ምን ይመስሉ እንደነበር፥ በዚያም ጊዜ ምን ቁም ነገር እንደተፈጸመ፥ የራቀውን አቅርበው ከዛሬው ጋር አገናዝበው፥ ትንቢታዊውንም ዘመን ከዛሬው ጋር በማገናኘት የታሪክን ሂደት በሁኔታው በዓይነቱ ተከታትለው ጽፈው ፈርመው፥ አትመውም ያስረከቡን አባቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ክቡር ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ አንደኛው ናቸው። . . .

አባ መልከ ጼዴቅ፥ ሊቀ ጳጳስ

ተጨማሪ ይመልከቱ

. . . ይህን መጽሐፋቸውን በእውነቱ፥ ከራሳቸውም የሕይወት ታሪክ ባሻገር፥ ባጠቃላይ የኢትዮጵያን ጥንታዊ የትምህርትና የልጅ አስተዳደግ ሥነ ሥርዓት በዝርዝር እንደሚያስተምር ትልቅ መዝገብ ልናየው እንችላለን። . . .

ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት

ተጨማሪ ይመልከቱ

. . . የመርስዔ ኀዘን መጻሕፍት ለአንባብያን፥ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ ትምህርትን፥ ለተመራማሪዎች መነቃቃትን፥ ለባህል የመስክ ሠራተኞች ደግሞ ትጋትን ይቸራሉ ብዬ ተስፋ የማደርገው። . . .

ዶክተር ፈቃደ አዘዘ

ተጨማሪ ይመልከቱ