የኢትዮጵያና የእንግሊዝ ሶማሌላንድ የወሰን መካለል ታሪክ

rsz_book_4_use_this

. . . አሁን ለአንባቢ በቀረበው መጽሐፍ ውስጥ በዝርዝር የተገለጸው የኢትዮጵያና የእንግሊዝ ሶማሊላንድ የወሰን መደንገግ ታሪክ የተለየ አብነት አለው። ይኸውም ወሰኑ መደንገጉ ብቻ ሳይሆን ሂደቱ በሚያስገርም ምልኣትና ጥንቃቄ መተረኩ ነው። መተረኩ ብቻ ሳይሆን ትረካው ከኢትዮጵያ ወገን፣ በኢትዮጵያዊ ቋንቋ መሆኑ ነው። . . .

ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ

ተጨማሪ ይመልከቱ

. . .ለእኔ ትውልድ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ አዲስ ሰው አይደሉም። ገና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በነበርንበት ጊዜ «የአማርኛ ሰዋስው» የሚለው መጽሐፋቸው መማሪያችን ስለነበረ ከስማቸው ጋር በደንብ እንተዋወቃለን፤ . . .

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም

ተጨማሪ ይመልከቱ