Book 2 Blurb 1 tamrat

ክቡርብላታመርስዔኀዘንወልደቂርቆስ፣ ለኢትዮጵያሕዝብብዙታላላቅውለታአስመዝግበውያለፉ፥ ከፍተኛየትምህርትናየባህልመሪመሆናቸውንየማያውቅየሚኖርአይመስለኝም። በተለይ፤ የተፈሪመኰንንትምህርትቤትሲቋቋም፥ የመጀመሪያውየግእዝናየአማርኛአስተማሪበነበሩበትጊዜባዘጋጁትየአማርኛሰዋስውያልተጠቀመተማሪአይገኝም። በዚህምክንያት፥ የሳቸውስምናዝና፥ ከልጅነታችንጀምሮበአእምሯችንተቀርፆይኖራል። በቅርቡ፥ በልጃቸውበአቶአምኃጠንቃቃአዘጋጅነት፥ አዲስአበባዩኒቨርሲቲያሳተመላቸው፥ የሐያኛውክፍለዘመንመባቻ: የዘመንታሪክትዝታዬ፥ ካየሁትናከሰማሁት 1896-1922 የተሰኘውመጽሐፋቸው፥ ለሁልጊዜየሚቆይትልቅሐውልትሆኖላቸዋል። አሁንደግሞ፥ ይህንን፥ ትዝታዬ፥ ስለራሴየማስታውሰውበሚልርእስየጻፉትን፥ የግልሕይወትታሪካቸውን፥ ይኸውየተባረከልጃቸውበጥራትአዘጋጅቶአቅርቦልናል።

ይህንመጽሐፋቸውንበእውነቱ፥ ከራሳቸውምየሕይወትታሪክባሻገር፥ ባጠቃላይየIትዮጵያንጥንታዊየትምህርትናየልጅአስተዳደግሥነሥርዓትበዝርዝርእንደሚያስተምርትልቅመዝገብልናየውእንችላለን። የንባብትምህርት፥ በጅሩገጠርበሚገኝያያቶቻቸውቤተክርስቲያን፤ ዜማደግሞ፥ በድጓመምህርነታቸውበጣምይከበሩበነበሩትአባታቸው፥ በአለቃወልደቂርቆስቀጥተኛቁጥጥርሥር፤ ቅኔ፥ ጻድቁአቡነዜናማርቆስባቋቋሙትየደብረብሥራትገዳም፤ እንደዚሁምየመጻሕፍትትርጓሜ፥ ዝናቸውእስከቤተመንግሥትድረስከታወቀላቸውታላላቅመምህራን፥ የተሟላሥልጠናአግኘተዋል። እንደዚህበየደረጃውያለፉበትንየትምህርትናየመልካምአስተዳደግመንገድብቻሳይሆን፣ በጊዜውስለነበሩየማህበራዊናጠቅላላየሀገርጉዳዮችምበየስፍራውይጠቃቅሳሉ። ይልቁንም፥ በሌላቦታየማይገኝ፥ ስለኢትዮጵያጥንታዊየትምህርትዓይነቶችናስለይዘታቸውየተጣራዝርዝርመግለጫበዚህመጽሐፍመጨረሻላይቀርቦልናል።

ደራሲው፥ በብዙነገሮችየመጀመሪያየመሆንእድልአጋጥሟቸዋል! በተፈሪመኰንንትምህርትቤትየመጀመሪያውየአማርኛናየግእዝቋንቋመምህርነበሩ። እንደዚሁም፥ በጅጅጋከተማ፥ በራስመኰንንስምተሰይሞየነበረውንየመጀመሪያውንትምህርትቤትአቋቁመው፥ የመጀመሪያውዲሬክተርሆኖየመምራትእድልያገኙትእሳቸውናቸው።

ይህየትዝታመጽሐፍ፥ 1922 ዓምላይነውየሚቆመው።በመሆኑምየደራሲውየራሳቸው፥ከ40ዓመትየሚበልጥየሕይወትታሪካቸውእዚህአልተሸፈነምማለትነው።ነገርግን፥በነዚህአያሌዓመታትውስጥነበር፥እስከአፄኃይለሥላሴዘመነመንግሥትተፍጻሜትድረስ፥ለአገራቸውከፍተኛአገልግሎትያበረከቱት! በተለይየIትዮጵያቤተክርስቲያንከግብፁየእስክንድርያፕትርክናነፃነቷንእንድታገኝበተደረገውዘዲያማዲፕሎማሲ፤በብሔራዊውፓርላማሥራእድገትና፥በተለያዩየተምህርትናየባህልድርጅቶችዓይነተኛየአመራርአስተዋፅኦያበረከቱትበነዚሁዓመታትነበር! በውነቱክቡርብላታመርስዔኀዘን፥የነዚህንምዓመታትታሪክቢሸፍኑልንኖሮ፥በቅርብታሪካዊዘገባእጅግበጣምየተራቆተውንየንጉሠነገሥቱንውስጣዊህልውናታሪክምጭምር፥እግረመንገዳቸውንበሚገባሳያብራሩልንአይቀሩምነበር!