ቀዳሚቃል


ኢትዮጵያ ሊቃውንትአራቱንብሔራዊየትምህርትዓይነቶችበዕውቀትያጠቃለለውንመምህር “አራትዓይና” ይሉታል። የትምህርታችንሥርዓትእንደሚያስረዳውየአንድመምህርግዴታከመምህሩየወረሰውንዕውቀትለደቀመዝሙሩእንዳለ (ሳይቀንስሳይጨምር) ማውረስነው። የብሔራዊዕውቀታችንንመጠንከአራቱዓይነትዕውቀቶችአልፎበየዘመኑእያደገእንዲሄድያደረገውአንዳንድእንደክቡርብላታመርስዔሐዘንወልደቂርቆስያሉየወረሱትየማያጠግባቸውአምስትዓይናሊባሉየሚገባቸውተመራማሪምሁራንጥረትነው። እነዚህ “አምስትዓይና’’ ሊቃውንትአእምሯቸውሁልጊዜስለሚራብዕውቀትፍለጋበሁሉቦታይገኛሉ። የውጭሀገርፈላስፎች፥ የውጭሀገርታሪክጸሐፊዎች፥ የውጭሀገርድርሰቶችወደሀገራችንቋንቋየተመለሱትበእነዚህተመራማሪዎችየዕውቀትጥማትነው።
በእኛዘመንየኢትዮጵያንዕውቀትበማዳበርረገድየአንደኛነቱንቦታየያዙትአምስትዓይናውብላታመርስዔሐዘንወልደቂርቆስናቸው። የትምህርትጓደኞቻቸውታላቅደብርየሚያስሾምትምህርትሲመርጡክቡርብላታመርስዔሐዘንየመረጡትየሚማረውናየሚያስተምረውአጥቶሊጠፋየነበረውንትምህርትነበር። ለአማርኛቋንቋሰዋስውበማውጣትፈርየቀደዱትክቡርብላታመርስዔሐዘንናቸው።
ክቡርነታቸውየትምቦታለምንምጉዳይቢሄዱዕውቀትሳይዘርፉአይመለሱም። በኢትዮጵያናበግብጽቅብጦችመካከልተፈጥሮለነበረውችግርመፍትሔፍለጋብዙዎችእንደክቡርብላታመርስዔሐዘንወደግብጽሄደውነበር፤ ዝርዝሩንከሥርመሠረቱየምናውቀውግንክቡርነታቸውከጻፈልንመረጃነው። አንኮበርደርሰውሲመለሱባዶእጃቸውንአልመጡም። የወይዘሮዘውዲቱየንግሥበዓልላይየተገኘሁሉበሚጠፋውግብዣላይሲያተኩርክቡርነታቸውየሚወረስዕውቀትይሰበስብነበር።
ጅጅጋየራስመኰንንትምህርትቤትሥራአስኪያጅነትቢሾሙመጽሐፈዜናዓመት ዘ፲፱፻፳፭ ዓ. ም. የሚባልብዙታሪክየያዘዘገባሰጡን። ልጆችበርቱእንማር፤ ባገርፍቅርእንጠንክር፤ ብርሃንሳለባንራመድ፥ አይረባንምየሌትመንገድ፤ እያሉልጆቹንሀገርፍቅርያስተምሩነበር። ፊታውራሪበየነመርድናወይዘሮሮማነወርቅተፈሪበተክሊልሲጋቡከቦታውቢገኙዝርዝሩንበመመዝገብየተክሊልሥርዓትምንአንደሚመስልአስተማሩን። ወልወልላይከፋሺስቶችጋርስለተነሣውግጭትከኢትዮጵያበኩልምንይባልእንደነበረየምናውቀውገናየክቡርብላታመርስዔሐዘንወልደቂርቆስዘገባሲታተምነው። የደጃዝማችተሾመሸንቁጥንየአርበኝነትታሪክምክንያትበማድረግ፥ በሙሉሸዋበመንዝናበመርሐቤቴአውራጃየተደረገውንየአርበኞችጦርነትናውጤቱንመዝግበውልናል። እነዚህንድርሰቶችያነሣሣኋቸውየክቡርነታቸውንማንነትለማሳየትእንጂድርሰቶቻቸውንዘርዝሮለመጨርስአይደለም።
የባሕረሐሳብስሌትየተከበረዕውቀትነው። ስሌቱንየሚያውቁትጥቂቶችሲሆኑአንዱክቡርብላታመርስዔሐዘንወልደቂርቆስመሆናቸውአያስገርምም። እሳቸውንከሌሎቹየባሕረሐሳብስሌትዐዋቂዎችየሚለያቸውያውዕውቀትየማዳበርፍላጎታቸውእዚህምላይመታየቱነው። ይኸምበዚህመጽሐፍውስጥበሁለትመልክይታያል፤ አንደኛ፥ ሲወርድሲዋረድከእኛዘመንየደረሰውንየባሕረሐሳብስሌትበአጭሩከአስተማሩንበኋላ፥ ለሰባዓመታትየሚያገለግሉዓመተምሕረትንከዓመተእግዚእ (AD) እናከዓመተተንባላት (ዓመተሂጅራ፥ ዓመተአጋር) ጋርየሚያገናዝቡሰንጠረዦችአዘጋጅተውልናል። ሁለተኛ፥ በሀገራችንያልነበረውንየዓመተተንባላትንአወጣጥስሌትአምጥተውልናል። የኢትዮጵያሙስሊሞችበዓመተተንባላትስለሚጠቀሙ፥ በዚህአስተዋፃኦዋቸውየነበረውንብሐራዊችግርአቃልለዋል። ይህክቡርነታቸውያቃለለውችግርየቱንያህልእንደሆነ፥ በ፲፱፻፷፩ ዓ. ም. ከየመንግሥትሠራተኞችማስተዳደሪያጠቅላይመሥሪያቤትየተጻፈላቸውጥያቄናክቡርነታቸውየሰጡትመልስያስረዳሉ። የደብዳቤዎቹፎቶግራፍበአባሪመልክበዚህመጽሐፍውስጥይገኛሉ። አገሪቷንያለአንድተጠያቂሊቅየማይረሳትአምላክክብርናምስጋናይድረሰው።
የሀገሪቱትምህርትየዓመተተንባላትንስሌትመጨመርእንዳለበትግልጽነበር፤ ምክንያቱምሊቃውንቱየአንድንድርጊትዘመንሲጽፉዘመኑንአንዳንድጊዜበዓመተተንባላትጭምርይመዘግቡታል። ስሌቱንግንማንምሊቅከሌሎቹየባሕረሐሳብስሌቶችጋርአላስተማረንም። ክቡርብላታመርስዔሐዘንየዕውቀቱንአስፈላጊነትበመገንዘባቸውስናደንቃቸው፥ ዕውቀቱንበተለመደውየዕውቀትጥማታቸውከሚገኝበትፈልገውአምጥተውታል። ከየትናእንዴትእንዳግኙትእንዲህሲሉይነግሩናል፤
ሊቃውንትአንዱንየዘመንቊጥርከሌላውጋርበማነጻጸርወይምበማገናዘብየሚጽፉት፤ ጉዳዩንበሁለትናበሦስትምስክርለማረጋገጥመሆኑየታወቀነው። እኔምለምስክርነትየቀረቡትንጥቅሶችለመረዳትስለፈለግሁስለዓመተተንባላትሥርዓተብተትግብጻውያንወዳጆቼንበመጠየቅናመጻሕፍትንበመመልከትጥናትጀመርኩ።
ጥናቶችለኅትመትካልበቁየጋንውስጥመብራቶችናቸው። ብዙዎቹየክቡርብላታመርስዔሐዘንድርሰቶችከተከተቱበትሳይወጡናተማሪዎችዕውቀታቸውንሳያዳብሩባቸውብዙዓመታትአልፈዋል። አሁንምልጃቸውአቶአምኃመርስዔሐዘንየአባቱንብሔራዊአስተዋፅኦለኢትዮጵያሕዝብለማቅረብበብሔራዊቁጭትባይነሣኖሮድርሰቶቹከተከተቱበትሳይወጡሌሎችብዙዓመታትሊያሳልፉምናልባትምሊጠፉይችሉነበር። አቶአምኃድርሰቶቹንለኅትመትበሚያዘጋጅበትጊዜእንነጋገርናእንጻጻፍስለነበረ፥ እኔምመጽሐፍለማሳተምሲሞከርየሚገጥሙትንችግሮችበግሌስለማውቅ፥ ከዚህለማድረስብዙእንቅፋትአንዳጋጠመውናሁሉንምበትዕግሥትናበጭካኔእንዳለፋቸውልመሰክርእችላለሁ። አቶአምኃለመታከትናለችግርሳይሸነፍየክቡርነታቸውንመጻሕፍትበእጃችንእንዲገቡስላደረገከልብየመነጨምስጋናይገባዋል።
ጌታቸውኃይሌ