Book 2 Blurb 1 tamrat

ክቡርብላታመርስዔኀዘንወልደቂርቆስ፣ ለኢትዮጵያሕዝብብዙታላላቅውለታአስመዝግበውያለፉ፥ ከፍተኛየትምህርትናየባህልመሪመሆናቸውንየማያውቅየሚኖርአይመስለኝም። በተለይ፤ የተፈሪመኰንንትምህርትቤትሲቋቋም፥ የመጀመሪያውየግእዝናየአማርኛአስተማሪበነበሩበትጊዜባዘጋጁትየአማርኛሰዋስውያልተጠቀመተማሪአይገኝም። በዚህምክንያት፥ የሳቸውስምናዝና፥ ከልጅነታችንጀምሮበአእምሯችንተቀርፆይኖራል። በቅርቡ፥ በልጃቸውበአቶአምኃጠንቃቃአዘጋጅነት፥ አዲስአበባዩኒቨርሲቲያሳተመላቸው፥ የሐያኛውክፍለዘመንመባቻ: የዘመንታሪክትዝታዬ፥ ካየሁትናከሰማሁት 1896-1922 የተሰኘውመጽሐፋቸው፥ ለሁልጊዜየሚቆይትልቅሐውልትሆኖላቸዋል። አሁንደግሞ፥ ይህንን፥ ትዝታዬ፥ ስለራሴየማስታውሰውበሚልርእስየጻፉትን፥ የግልሕይወትታሪካቸውን፥ ይኸውየተባረከልጃቸውበጥራትአዘጋጅቶአቅርቦልናል።

ይህንመጽሐፋቸውንበእውነቱ፥ ከራሳቸውምየሕይወትታሪክባሻገር፥ ባጠቃላይየIትዮጵያንጥንታዊየትምህርትናየልጅአስተዳደግሥነሥርዓትበዝርዝርእንደሚያስተምርትልቅመዝገብ
ልናየውእንችላለን። የንባብትምህርት፥ በጅሩገጠርበሚገኝያያቶቻቸውቤተክርስቲያን፤ ዜማደግሞ፥ በድጓመምህርነታቸውበጣምይከበሩበነበሩትአባታቸው፥ በአለቃወልደቂርቆስቀጥተኛቁጥጥርሥር፤ ቅኔ፥ ጻድቁአቡነዜናማርቆስባቋቋሙትየደብረብሥራትገዳም፤ እንደዚሁምየመጻሕፍትትርጓሜ፥ ዝናቸውእስከቤተመንግሥትድረስከታወቀላቸውታላላቅመምህራን፥ የተሟላሥልጠናአግኘተዋል። እንደዚህበየደረጃውያለፉበትንየትምህርትናየመልካምአስተዳደግመንገድብቻሳይሆን፣ በጊዜውስለነበሩየማህበራዊናጠቅላላየሀገርጉዳዮችምበየስፍራውይጠቃቅሳሉ። ይልቁንም፥ በሌላቦታየማይገኝ፥ ስለኢትዮጵያጥንታዊየትምህርትዓይነቶችናስለይዘታቸውየተጣራዝርዝርመግለጫበዚህመጽሐፍመጨረሻላይቀርቦልናል።

ደራሲው፥ በብዙነገሮችየመጀመሪያየመሆንእድልአጋጥሟቸዋል! በተፈሪመኰንንትምህርትቤትየመጀመሪያውየአማርኛናየግእዝቋንቋመምህርነበሩ። እንደዚሁም፥ በጅጅጋከተማ፥ በራስመኰንንስምተሰይሞየነበረውንየመጀመሪያውንትምህርትቤትአቋቁመው፥ የመጀመሪያውዲሬክተርሆኖየመምራትእድልያገኙትእሳቸውናቸው።

ይህየትዝታመጽሐፍ፥ 1922 ዓምላይነውየሚቆመው።በመሆኑምየደራሲውየራሳቸው፥ከ40ዓመትየሚበልጥየሕይወትታሪካቸውእዚህአል
ተሸፈነምማለትነው።ነገርግን፥በነዚህአያሌዓመታትውስጥነበር፥እስከአፄኃይለሥላሴዘመነመንግሥትተፍጻሜ
ትድረስ፥ለአገራቸውከፍተኛአገልግሎትያበረከቱት!በተለይየIትዮጵያቤተክርስቲያንከግብፁየእስክንድርያፕትርክናነፃነቷንእንድታገኝበተደረገውዘዲያማዲፕሎ
ማሲ፤በብሔራዊውፓርላማሥራእድገትና፥በተለያዩየተምህርትናየባህልድርጅቶችዓይነተኛየአመራርአስተዋፅኦ
ያበረከቱትበነዚሁዓመታትነበርበውነቱክቡርብላታመርስዔኀዘን፥የነዚህንምዓመታትታሪክቢሸፍኑልንኖሮ፥በቅ
ርብታሪካዊዘገባእጅግበጣምየተራቆተውንየንጉሠነገሥቱንውስጣዊህልውናታሪክምጭምር፥እግረመንገዳቸውን
በሚገባሳያብራሩልንአይቀሩምነበር!